Monday, November 9, 2009

ህዝብ፡ ለምኔ!

ሓይሉ ሻውል
ገና ያኔ፡ ከመነሻው፣
ነበረ ያካሄዱ ፡ዉሉ፡ የጠፋው፣
መ አ ሕ ድ፡ ብሎ ፡ ጀመረ፣
መስሎ፡ የአማራው፡ ጠበቃ፣
ወዲያው ደግሞ ሊተናነቅ፣
ከአንጋፋው፣ ከመስራቹ፣ ፕሮፌሰር፡
አስራት ወልደየስ፣
ላንቃ ፡ ለላንቃ፣
ከዚያ፡ ደግሞ፡ ገሸሽ፡ አለ፣
ቆምኩለት፡ ካለው፡ ዓላማ፣
ብዙም፡ ሳይቆይ፡ ተመለሰ፣
የስልጣን፣ ጥሙን፣ ለማርካት፣
ሲታሰሩለት፣
ፐሮፌሰር፡ አስራት፣
አምሶና፡ አብጠልጥሎ፣
ድርጅቱን፣ መአሕድን፣
ብቅ፡ አለ፡ ደግሞ፡ ይዞ፡
አዲሱን፡ መኢአድን
አፍታም፡ ሳይቆይ፣
ደግሞ አለ፣
ተጣመርኩኝ፡ ከሕብረት፡ ሀይሎች፣
ግን፡ ወራት፡ እንኩዋን፡ አልሞሉም፣
አኩርፎ፡ ሲኮበልል፣
ከህብረቱ፣
ስልጣንን፡ በማጣቱ፣
ቀጠለ፣ የእውር፡ ድንብሩን፣
ደግሞ፡ ሌላ፡ ድንገት፡ ቢገኝ፣
ጠጋ፡ ብሎ፡ የሚቃኝበት፡
የስልጣን፡ ጥሙን፡ ለማርካት፣
መጣለታ፡ ቅንጅት፣
በሩን፡ ወለል፡ አድርጎ፡ከፍቶ፡
ጋበዘው፡
እንዲወጣ፡ የድርሻውን፣
ለዲሞክራሲ፡ ግንባታ፡
ቅንጅት፡ በዚያ፡ አላበቃም፣
እንዲያውም፡ ሰጠው፡ ስልጣን፣
የመሪነቱን፣
ነገር፡ ግን፤ የተገኘውን፡
በእርሱ፡ መሪነት፡ ሳይሆን፡
በሌሎች፡ ብልሆች፡ ብርታት
የ 97ቱን፡ ምርጫ፡ ድል፣
አሰቀለበሰው፣ ሓይሉ፡ ሻውል፣
ይኸ፡ የሰው፡ አጉዋጉል፣
ጉዋደኞቹን፡ ለመበቀል፣
ልብ፡ በሉ፡ ወገኖቼ፣
ሓይሉ፡ ሻውል፡
ይኽ፡ አንደበተ፡ ጎደሎ፡
በደርግም፡ ሰልጣን፡ ነበረው፣
ያበረበት፡ ከአምባገነን፣
ልጆቼን፡ ላሳድግ፡ብሎ፡
ይኸው፡ ዛሬም፡ ተፈራርሙዋል፣
ከ አምባገነኑ፡ እና፡ ከዘር፡ አጥፊው፡
ከወያኔ
በሃብት፡ ላይ፡ ሃብት፡ ለማፍራት፣
ስልጣንም፡ ለመቀራመት፣
ብሎ፡
ህዝብ፡ ለምኔ!